Performance

የባህርዳር ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል በግራፊክስ ዲዛይንና ዲጂታል ማርኬቲንግ

October 26, 2026 | admin
የባህርዳር ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል በግራፊክስ ዲዛይንና ዲጂታል ማርኬቲንግ

የባህርዳር ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል በግራፊክስ ዲዛይንና ዲጂታል ማርኬቲንግ ያሰለጠናቸውን ሴት ወጣቶች አስመረቀ!

EMYC | ጥቅምት 15፣ 2019 ዓ.ል | ጀማዱል አወል 14፣ 1448 ዓ.ሂ

የአማራ ክልል ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ባህርዳር ቅርንጫፍ ለሁለት ወራት በግራፊክስ ዲዛይንና ዲጂታል ማርኬቲንግ ሲያሰለጥናቸው የቆየውን 17 ሴት ወጣቶች አስመረቀ።

ስልጠናው ሴት ወጣቶች የቴክኖሎጂ እውቀታቸውንና ተግባራዊ ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩ፣ በሙያው እንዲበቁ፣ የሥራ ዕድል እንዲፈጥሩና በኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ ንቁ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ለማስቻል ያለመ ነው።

በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ ለተመራቂዎቹ የሥራ ዕድል ለማመቻቸት የሚያግዙ ተቋማት ቃል የገቡ ሲሆን፣ ይህም ተመራቂዎቹ ያገኙትን እውቀትና ክህሎት በተግባር እንዲያውሉና ወደ ሥራ ዓለም እንዲቀላቀሉ የሚያግዝ ነው።

የአማራ ክልል ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ባህርዳር ቅርንጫፍ ወጣቶችን በሙያና በክህሎት በማብቃት፣ የሥራ ዕድል እንዲፈጥሩና ለማኅበረሰቡ ልማት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ ይቀጥላል።